Fana: At a Speed of Life!

የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመከተል መፈጸም ይገባል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በመንግሥት የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመከተል በላቀ ውጤት መፈጸም ይገባል አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፡፡

በክልሉ በበጀት ዓመቱ በልዩ ንቅናቄ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከክልሉ አጠቃላይ አመራር ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የመወያያ ሐሳብ ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)÷ አመራሩ ፍጥነት የታከለበትን ፈጠራ በመከተል ተግባራት በላቀ ደረጃ መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋል።

በክልሉ የተጀመሩ ተግባራትን እምርታዊ በሆነ መልኩ ለመፈጸም ፈጠራ ብቻውን በቂ አለመሆኑን ገልጸው÷ ፍጥነት እና የቀደሙት ጋር ለመስተካከል መረባረብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የፈጠራ እውቀት የሚያበረታታ መሆኑን አንስተው÷ በግሉ ዘርፍ ያልተሸፈኑ የገበያ ችግሮችን በመለየት ክፍተቱን እየሞላ እንደሆነና በሂደትም የግሉን ዘርፍ በማብቃት እያሸጋገረ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በመደመር መንግሥት ዕይታ ቅኝት በተለዩ ዘርፎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ የክልሉን ኢኮኖሚ ማሳደግና የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት ማሻሻል እንደሚቻል ጠቁመዋል።

በክልሉ በተለይም ለግብርናና የገጠር ሽግግር አስቻይ ሁኔታዎች መኖሩን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ይህንን መልካም አጋጣሚ በተገቢው በልማት ማዋል በዘርፉ እምርታዊ ለውጥ ማስመዝገብ ይገባል ብለዋል።

ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑና ኢንቨስትመንት እንዲጨምር በትኩረት መስራት እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሽግግር ማሳለጥ እንደሚገባ አጽንኦት መስጠታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.