በሐረሪ ክልል በ67 ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሚደረገው የተማሪዎች ምገባ መርሐ ግብር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ በሚገኙ የከተማና ገጠር ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች የምገባ መርሐ ግብር አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ በሚገኙ 67 ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ በሚደረገው የምገባ መርሐ ግብር ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።
የምገባ መርሐ ግብሩ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ፣ በትምህርት ላይ ያሉ ትምህርት እንዳያቋርጡና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም የትምህርት ተሳትፎን ከማሳደግ ባለፈ የተማሪዎች የትምህርት ቅበላና ጥራትን በማጎልበትና ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በማስቻል መቀጨጭና መቀንጨርን እንደሚያስቀር ገልጸው÷ በክህሎት፣ እውቀት፣ አመለካከት እና ስነ ምግባር የታነፀ አምራች ዜጋ ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።
የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የትምህርት ቤት ምገባ አቅርቦትን ለማጎልበት ይሰራል ያሉት አቶ ኦርዲን÷ የተማሪ ወላጆች ባለሃብቶችና ሌሎችም አካላት የትምህርት ቤት ምገባውን ሊደግፉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ከሚያከናውናቸው ሰው ተኮር ስራዎች ውስጥ የትምህርት ቤት ምገባ አንዱ መሆኑን በማመላከት በክልሉ ያለውን ፀጋ በመጠቀም መርሐ ግብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!