Fana: At a Speed of Life!

ኢራን የሚሳኤልና ድሮን ዐውደ ርዕይ አዘጋጀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባለስቲክ ሚሳኤሎች እና የድሮኖች ዐውደ ርዕይ በቴህራን አዘጋጅቷል።

ኢራን ለዕይታ ያቀረበቻቸው የጦር መሳሪያዎች የሀገሪቱን የመከላከያ ዓቅም ለማሳደግ የታጠቀቻቸውን የጦር መሳሪያ የሚያሳዩ እንደሆኑ ዩሮኒውስ ዘግቧል።

ሀገሪቱ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ከእስራኤል ጋር ከገባችበት ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ባለው ዐውደ ርዕይ ረጅም ርቀት ተወንጫፊ የባላስቲክ ሚሳኤሎች ቀርበው በህዝብ እየተጎበኙ ነው።

በዐውደ ርዕዩ ላይ አዳዲስ ድሮኖች እንዲሁም 1 ሺህ 700 ኪሎ ሜትር እና 2 ሺህ ኪሎ ሜትር መምዘግዘግ የሚችሉ ኢማድ እና ኮራምሻህር ባላስቲክ ሚሳኤሎች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

በተጨማሪም እጅግ በጣም ፈጣን መሆኑ የተነገረላቸው ፋታህ 1 እና ፋታህ 2 ሀገር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤሎች በጉብኝቱ ታይተዋል፡፡

በዐውደ ርዕዩ ተገኝተው የጦር መሳሪያዎቹን የተመለከቱ ኢራናውያን በሀገራቸው የመከላከያ አቅም ላይ ያላቸው በራስ መተማመን ሊጨምር መቻሉን ተናግረዋል።

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.