Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ባለሃብቶችን ለመሳብ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በተያዘው በጀት ዓመት በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

ያሉትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች ወደ ልማት ለማስገባት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ታሪኩ÷ ግብርናና ኢንዱስትሪን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ የኢንቨስትመንት አመራጮች መኖሩን አስረድተዋል፡፡

በቂ አቅምና ልምድ ያላቸውን ባለሃብቶች በመመልመልና በመምረጥ በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ለማድረግ መሬት ግልፅ፣ ወጥ፣ ፍትሃዊና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን አንስተዋል።

በተጠናቀቀው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በግብርና ዘርፍ 386 ሚሊየን 550 ሺህ ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 11 እንዲሁም በኢንዱስትሪ ዘርፍ 80 ሚሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 14 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ ወደ ስራ ለገቡ 69 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል እንደተደረገላቸውም ጠቅሰዋል።

ወደ ስራ ያልገቡ 21 ፕሮጀክቶች ደግሞ በአስቸኳይ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ማስጠንቀቂያ እንደተጣቸው ጠቁመዋል፡፡

ወደ ስራ በገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችም ለ615 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን አመላክተዋል።

በመጀመሪያ ሩብ ዓመት በኢንቨስትመንት ላይ ለተሰማሩ ባለሃብቶች 1 ሺህ 30 ሄክታር መሬት መተላለፉን አንስተው÷ ባለሃብቶች በገቡት ውል መሰረት የወሰዱትን ቦታ እንዲያለሙ ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቅ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ታሪኩ÷ ባለሃብቶች በክልሉ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች በመጠቀም መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.