Fana: At a Speed of Life!

ማዕከሉ በዘርፉ ለነበረ ቀና ቁጭት ምላሽ የሰጠ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የላቀ የሕክምና ማዕከል በዘርፉ ለነበረ ቀና ቁጭት ምላሽ የሰጠ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ እንዳሉት÷ በይፋ ተመርቆ ስራ የጀመረው ዘመናዊ የጤና ማዕከሉ÷ የዓለም አቀፍ ጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ዘመኑን የዋጀ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሟላ ነው።

ይህም ለባለሙያው፣ ለታካሚው እንዲሁም ለአስታማሚው ጭምር የተመቸ ዘመናዊ የጤና ማዕከል እንደሆነ እና በዘርፉ ለነበረ ቀና ቁጭት ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል።

የተለያዩ አገልግሎቶች የተካተቱበት የሕክምና ማዕከል በውስጡ፡-

👉 የተኝቶ ህክምና ህሙማን ክፍሎች (IPD)
👉 የጨረር ህክምና አገልግሎቶች

👉 ሲቲ-ስካን እና ኤክስሬይ
👉 የህፃናት እና የአዋቂዎች ፅኑ ህሙማን ክፍሎች (ICU)

👉 የኦክስጅን ማምረቻ ፕላንት
👉 የቪአይ ፒ አልጋዎች

👉 የኦፒዲ ክፍሎች
👉 የኦፕራሲዮን ክፍሎች(OR) እና የማገገሚያ ክፍሎች እንዲሁም

👉 የድንገተኛ ክፍል አልጋዎች
👉 በየህክምናው አይነትና በየወለሉ ፋርማሲ እና የመድሃኒት ስቶር
👉 ላቦራቶሪ

👉 የአስተዳደር ቢሮዎች
👉 የማብሰያ ክፍሎች፣ ዋና ካፊቴሪያ፣ በየወለሉ ለሚገለግሉ ባለሙያዎች የሚሆኑ ካፊቴሪያዎች

👉 የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ከውብ ምድረ ግቢ ጋር ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህን ለማሕበረሰቡ ፋይዳው እጅግ የላቀ የጤና ማዕከል ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል።

በማዕከሉ የሚገኙ ባለሙያዎች ለህሙማን የሚሰጡትን አገልግሎት የሚያቀልል የላቀ የሕክምና ማዕከሉን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ከምንም ጊዜ በላይ በሙያዊ ሥነምግባር እና ርህራሄ እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.