Fana: At a Speed of Life!

ዩክሬን 100 ተዋጊ ጄቶችን ከፈረንሳይ ልትረከብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩክሬን ፈረንሳይ ሰራሽ ራፋሌ ኤፍ 4 የተሰኙ 100 ተዋጊ ጄቶችን ከፈረንሳይ ለመግዛት ተፈራርማለች፡፡

ስምምነቱን የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የዩክሬን አቻቸው ቮልድሚር ዘለንስኪ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ፈረንሳይ በረጅም የክፍያ ጊዜ ለዩክሬን 100 ተዋጊ ጄቶችን፣ የአየር መቃወሚያዎችንና ሌሎች ወታደራዊ ቁሶችን ለዩክሬን የምታቀርብ ይሆናል፡፡

ቮሎድሚር ዘለንስኪ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ስምምነቱ ታሪካዊ ከመሆኑ ባሻገር የዩክሬንን ወታደራዊ አቅም ይበልጥ ለማጠናከር ያስችላል፡፡

የተዋጊ ጄቶች አቅርቦት በፈረንጆቹ 2035 የሚጠናቀቅ ሲሆን ÷ የሌሎች ወታደራዊ ቁሶች ደግሞ በተያዘው ዓመት እንደሚጀመር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.