የ2ኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሐ ግብር ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በዘጠኝ ክልሎች የሚተገብረው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሐ ግብር ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው።
ኢንስቲትዩቱ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ እንዳስታወቀው፤ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ በተተገበረው የመርሐ ግብሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ አበረታች ውጤት ተገኝቷል።
በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር፣ አካታች የእሴት ሰንሰለቶችን እና የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ማሳደግ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጠው ጠቁሟል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ተተግብሮ ገበያ ተኮር ኩታገጠም እርሻን ለማስፋት ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል።
የምዕራፍ ሁለት መርሐ ግብሩ ደግሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ሶማሌ ክልሎችን በማካተት በዘጠኝ ክልሎች 6 ነጥብ 5 ሚሊየን አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚተገበር ተመላክቷል።
በዚህም ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የማይበገር የሰብል እና የእንስሳት እርባታ ንግድ፣ ዲጂታል ግብርና፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ፣ የአቅም ግንባታ፣ የስርዓተ ምግብ እና የሰብአዊ ልማት ትስስርን ጨምሮ ዘጠኝ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ይተገበራል ተብሏል።
መርሐ ግብሩ የገጠር ማህበረሰቦች ዘላቂ የኢኮኖሚ እድሎችን በመፍጠር የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ ስለመሆኑም ተነግሯል።
በተለይም ገበያ ተኮር የሆኑ ሰብሎችን በኩታገጠም በማምረት የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ በሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሐ ግብር በስፋት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
በዚህም የአርሶ አደሮችን ኑሮ ማሻሻል፣ የምግብ ዋስትናን እና ተመጣጣኝ ዋጋን ማስፈን፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት፣ የወጪ ንግድን እና የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያን ማሳደግ እንዲሁም የሥራ ዕድል መፍጠር በትኩረት ይሰራባቸዋል።
በመርሐ ግብሩ ማስጀመሪያ የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮችና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን÷ በምዕራፍ አንድ የነበሩ አፈፃፀሞችን የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ ቀርቧል።
በመሳፍንት ብርሌ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!