Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር በትብብር ያዘጋጁት 14ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ፤ የተቀላጠፈና ጠንካራ የሆነ የንግድ ሥርዓትን በመፍጠር ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ልዩ ልዩ የእህል ዓይነቶች ተመርተው ለውጭ ገበያ መቅረባቸው ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዳደረጋት ተናግረዋል።

መንግስት ምርታማነትና የምርት ጥራትን ለማሳደግ በፖሊሲ የተደገፈ ስራ በመስራት ላይ እንደሆነ አብራርተው፤ ነጻ ገበያን በመፍጠር የውጪ ኢንቨስተሮች ተሳትፎን የማሳደግ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ሀገር በቀል የሆኑ ተቋማት በዘርፉ ተወዳዳሪነታቸው እንዲያድግ ድጋፍ እንደሚደረግም ነው ያብራሩት።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው፤ የዘርፉን አቅም በማውጣት ዓለም አቀፍ የገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የተሰራውን ስራ አድንቀዋል።

የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ምርት በዓለም አቀፍ ደረጃ በማደግ ላይ ያለ ወሳኝ ምርት በመሆኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ከፍተኛ የስራ ዕድል እየፈጠሩበት እንደሆነ አንስተዋል።

በዘርፉ ምርታማነትን ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም የዲጂታል መተግበሪያዎችን ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የጥራጥሬ እና የቅባት እህል ላኪዎች ማሕበር ፕሬዚዳንት አዳዊ አብዲ በበኩላቸው፤ በመንግስት ቁርጠኝነት በሚከናወነው የሪፎርም ስራ ዘርፉ በማደግ ላይ ነው ብለዋል።

ይህም የውጭ ገበያ ተወዳዳሪነት መጨመሩን ጠቅሰው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.