Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በስኬት እንዲከበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በስኬት እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተከናውኗል፡፡

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ከሕዳር 25 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል፡፡

የበዓሉ የጸጥታና ደህንነት ዓብይ ኮሚቴ አባላት በዛሬው ዕለት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም በዓሉ በስኬት እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተመላክቷል፡፡

አፈ ጉባዔ አገኘሁ የጸጥታና ደህንነት ዓብይ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በተሳካ ሁኔታ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አውስተዋል፡፡

በዓሉ ሕብረብሔራዊ አንድነትን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የሚከናወነውን አጠቃላይ ተግባር በተገቢው ሁኔታ መደገፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኮሚቴው እስካሁን ላከናወነው ውጤታማ የቅድመ ዝግጅት ሥራ አመስግነው÷ በዓሉ በድምቀት እንዲጠናቀቅ የጸጥታ ዘርፉ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የኮሚቴው አባላት በበኩላቸው÷ በዓሉ ለኢትዮጵያ ገጽታ ግንባታ፣ ለኢኮኖሚ መነቃቃት፣ ለሕዝቦች አንድነትና ትስስር መጠናከር ሚናው ጉልህ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ ማረጋገጣቸውንም የም/ቤቱ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.