Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ የማበልፀጊያ ማዕከላት ጥምረት ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ የማበልፀጊያ ማዕከላት ጥምረትን በዛሬ ዕለት በይፋ አቋቁሟል።

የጥምረቱ ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎች በተናጠል ያሉ ጥናትና ምርምሮቻቸውን በማበልጸግ በጋራ ወደ ገበያ ማውጣትና ማሳደግ እንደሆነ ተነግሯል።

የዩኒቨርሲቲዎች የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማበልፀጊያ ማዕከሎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማስቻል እገዛ ያደርጋል ተብሏል።

እንዲሁም ዩኒቨርስቲዎች በዘላቂነት ለሀገር ኢኮኖሚና ለሰው ሀይል ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።

የትምሕርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲዎች የፈጠራ ሃሳቦች መፍለቂያ በመሆናቸው የጥምረቱ መቋቋሙ ያግዛቸዋል።

የጥምረቱ መቋቋም ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ውስን ሀብቶች በጋራ ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዲያደርሱ እና በጋራ እንዲጠቀሙ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በምርምር ማዕከላት ሀሳቦች ከተረጋገጡ በኋላ ወደማበልፀጊያ ማዕከላቱ ገብተው ከፍ ያለ ደረጃ እንዲደርሱ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

በመድረኩ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች፣ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሲገኙ የተለያዩ ሀገራት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።

በሶስና አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.