ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ውይይታችን የባለብዙ ወገን ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም እንደ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ፣ ሰላም እና ፀጥታ፣ ዘላቂ ልማት ያሉ የጋራ ዓለም አቀፋዊ ትኩረታችንን በምናጠናክርበት መንገድ ላይ ያጠነጠነ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሊደረግ ስለሚችለው ድጋፍም ተወያይተናል ብለዋል በመልዕክታቸው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!