አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኢጋድ ዋና ጸኃፊ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸኃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አቅርበዋል።
ዋና ጸኃፊው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ ከአምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጋር በቀጣናዊ እና ተቋማዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የኢጋድን የጋራ አጀንዳ በመምራት ረገድ ትልቅ ሚና ወደሚጫወተው ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ አካል ወደሆነው የኢጋድ አምባሳደሮች ኮሚቴ መቀላቀላቸውንም ዋና ጸኃፊው ገልጸዋል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ሕዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!