Fana: At a Speed of Life!

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር ፈጣን ዕድገት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው – ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) መንግሥት ከሕብረተሰቡ ጋር ተባብሮ ሲሰራ ፈጣን ዕድገት ማምጣት እንደሚቻል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማሳያ ነው አሉ፡፡

ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት፤ ሆሳዕና ከተማ በሚያስደንቅ ፍጥነት ወደ ‘ስማርት ሲቲ’ ተለውጣለች።

ከ7 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰሩ የልማት ስራዎች ለወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ እና ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ የመስራት ባህልን የሚያዳብሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲሁም የአመራሩ ክትትል ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለ20ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የተደረገው ዝግጅት መልካም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚቻል ክልሉ ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፋንታሁን ሊራንሶ በበኩላቸው፤ ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል አበረታች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በከተማው ያለው ተነሳሽነትና መነቃቃት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.