ኢትዮጵያና ቻይና በጋራ የልማት ግቦች ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አጋርነት ገንብተዋል – ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ቻይና የጋራ የልማት ግቦች ላይ የተመሰረተ ጠንካራ አጋርነት ገንብተዋል አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)።
የኢትዮጵያ እና የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸው የተጀመረበትን 55ኛ ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመከባበር፣ በእኩልነት እና በጋራ የልማት ግቦች ላይ የተገነባ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው ÷ ቤጂንግ በኢትዮጵያ ልማት በተለይም በመሠረተ ልማትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ትገኛለች ነው ያሉት፡፡
ሀገራቱ በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ እና የቻይና አፍሪካ ትብብር መድረክን ጨምሮ በባለብዙ ወገን መድረኮች በትብብር እየሰሩ መሆኑን አብራርተዋል።
የሀገራቱ ግንኙነት ለደቡብ ደቡብ ትብብር አርአያ መሆኑን ያወሱት ሚኒስትሩ ÷ አሁን ላይ አጋርነታቸው ሁሉን አቀፍ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂካዊ የግንኙነት ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ትብብር ለማስፋት እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ አመላክቷል።
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በበኩላቸው ÷ ሁለቱ ሀገራት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ እና እየጠነከረ የመጣ ወዳጅነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ቻይና ባላቸው የ55 ዓመት የዲፕሎማሲ ግንኙነት እርስ በርስ በመደጋገፍ የትብብር ምሳሌ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ የሀገራቱ መሪዎች እየሰጡት ባለው ስትራቴጂካዊ አመራር ለሁለቱም ሕዝቦች እውነተኛ ጥቅም በሚያስገኝ መልኩ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በፍጥነት እያደገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የ55ኛ ዓመት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በዓልን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የሀገራቱን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ብሎም በመካከላቸው ያለውን ሁለንተናዊ አጋርነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!