Fana: At a Speed of Life!

ጤናማ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ወሳኝ ሚና ያለው የክትባት ተደራሽነት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር የክትባት ተደራሽነትን ማጠናከር ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ወሳኝ ሚና አለው አለ።
ህጻናት እንደተወለዱ የሚሰጠው የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአበበች ጎበና ሆስፒታል በይፋ ተጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ እንዳሉት፤ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ነው።
ከሚከናወኑት ተግባራት መካከል በሽታ መከላከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ የክትባት ተደራሽነትን ማጠናከር ላይ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የጉበት በሽታ በሀገሪቱ ከፍተኛ የጤና ችግር እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ችግሩን ለመከላከል ክትባትን ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ለበሽታው ተጋላጮች የመከላከያ ክትባት የመስጠት ሙከራ እንዳለ አንስተው፤ አሁን ላይ ህጻናት እንደተወለዱ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት አገልግሎት እንዲያገኙ ዝግጅት ተደርጎ ወደተግባር መገባቱን ገልጸዋል።
ጤናማ ማኅበረሰብን ለመፍጠር እየተደረገ ላለው ጥረት የዚህ የተጠናና ውጤታማ ክትባት መጀመር ወሳኝ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
ማኅበረሰቡ የክትባቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በተለይም እናቶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል።
ክትባቱ ሕፃናት በተወለዱ በ24 ሰዓታት ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል።
የጉበት በሽታ ከሚተላለፍባቸው ዋነኛ መንገዶች መካከል ከእናት ወደ ልጅ መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ በበኩላቸው፤ ሕፃናትን እንደተወለዱ ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግ ዋነኛ የመከላከያ መንገድ መሆኑን ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.