የኢትዮ-ቻይና የጉምሩክ አስተዳደር ትብብር …
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና የጉምሩክ አስተዳደር ተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ የተቋም ልማትና ፈጣን የጉምሩክ አገልግሎት መስጠት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ከቻይና ጉምሩክ አስተዳደር ሚኒስትር ዴኤታ ዋንግ ጁን ጋር ተወያይተዋል።
ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በወቅቱ እንዳሉት፤ የጉምሩክ አስተዳደር ትብብር የሁለቱን ሀገራት የቀደመ ወዳጅነት ይበልጥ ያጠናክራል።
የጉምሩክ አስተዳደር ልህቀትን ለማጠናከር ከቻይና ጋር መስራታችን ይበልጥ ውጤት እንድናመጣ ይረዳናል ብለዋል።
የቻይና ጉምሩክ አስተዳደር ሚኒስትር ዴኤታ ዋንግ ጁን በበኩላቸው ለኢትዮጵያ የጉምሩክ አስተዳደር ሪፎርም ሀገራቸው ልምዷን ለማካፈል ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በዙፋን አምባቸው