የሐረርን ታሪክና ቀደምት ሥልጣኔ የሚመጥኑ ሥራዎች…
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕዝብን በማስተባበር እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች ሐረር ቀደምት ስልጣኔዋን በሚመጥን ደረጃ ላይ እንድትገኝ እያስቻሉ ነው አለ የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፡፡
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እንዳሉት ÷ ሐረር ከተማ የዘመናዊ ከተሜነትን እሳቤ ቀድሞ በመተግበር ከሚጠቀሱት ግንባር ቀደም ከተሞች መካከል ናት።
ይሁን እንጅ በተለይም ከለውጡ መንግሥት በፊት ለውጥን እንደናፈቀች የሕዝቦቿም የመልማት ፍላጎት ከምኞት መሻገር ሳይችል መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
ከለውጡ መንግሥት ወዲህ ግን ከተማዋን የማዘመን ተግባራት አርዓያ በሚሆን መልኩ እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
ከኮሪደር ልማቱ ጅማሮ ማግስት የክልሉ መንግሥት የአካባቢያዊ ፀጋዎችንና አቅሞችን መነሻ ያደረጉ ውጤታማ ሥራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡
በአነስተኛ ወጪ፣ በላቀ የአመራር ጥበብ እና ቁርጠኝነት ሕዝብን በማስተባበር እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች የከተማዋን ታሪክና ቀደምት ሥልጣኔ በሚመጥን ደረጃ እንድትገኝ የሚያስችሉ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ሐረር ዛሬ በይበልጥ መነቃቃቷን የገለጹት ኃላፊው ÷ ወደ ኋላ የቀረችባቸው ዓመታትን ለመካስ በሚያስችል ደረጃ ቀንና ሌሊት እየተሠራ እንደሆነ ነው የገለጹት።
የኮሪደር ልማት ሥራው ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ውብና ማራኪ እንድትሆን ማስቻሉን ጠቁመው÷ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት እጅ ለእጅ በመያያዝ እያኖሩት የሚገኘው አዲስ የስኬት ታሪክ የከተማውን ውበት በመግለጥ የክልሉን እምቅ የቱሪዝም አቅም ለመጠቀም ያገዘ ነው ብለዋል።
እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደፈጠረና እና ከፅዳት መጓደል ጋር በተያያዘ ሲስተዋሉ የቆዩ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድም ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱን አረጋግጠዋል።
በሐረር ከተማ ቀን ከሌሊት በመሥራት በአጭር ጊዜ የተገኘው ውጤትና የተመዘገበው ስኬትም የሥራ ባህልን የቀየረና የይቻላል መንፈስን ያሰረፀ ሆኗልም ነው ያሉት።
የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በሚያሳድግ መልኩ እየተሠሩ የሚገኙ ሥራዎችና የታዩ ውጤቶችም የሐረርን ገናናነት ዳግም እውን ማድረግ እንደሚቻል አመላካች ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!