Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የግብር ከፋዮችን ቅሬታ አጣርቶ ምላሽ የሚሰጥ አሰራር ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግብር ከፋዮችን ቅሬታ ሃላፊዎች በተገኙበት አጣርቶ ምላሽ መስጠት የሚያስችል አሰራር ከመጪው ሐሙስ ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

በአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚኖርን ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ጽ/ቤት ሥር ተዋቅሯል።

አሰራሩ በአስተዳደሩ የገቢዎች ቢሮ ስር በተዘረጋው የቅሬታ አፈታት ሥርዓት ያልረኩ ግብር ከፋዮች ቅሬታዎቻቸውን የሚያቀርቡበት ነው፡፡

በዚህ መሰረትም ከገቢ አሰባሰብ፣ ከሠራተኞች ሥነ ምግባርና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ ቅሬታዎች ዘወትር ሐሙስ ሃላፊዎች በተገኙበት የሚደመጡና ተጣርተው ምላሽ የሚሰጥባቸው ይሆናል፡፡

የተዘረጋው አሰራር ለከንቲባ ጽ/ቤት በሚስጢር ጥቆማ ከሚሰጥበት ነጻ የጥሪ ማዕከል 9977 እና የሚስጢር ሳጥን በተጨማሪ ቅሬታዎችን በአካል ለበላይ አመራር ማቅረብ ያስችላል፡፡

አሰራሩ ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ወደ ተግባር እንደሚገባ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለሆነም ከመጪው ሐሙስ ሕዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከገቢዎች ጋር ብቻ የተያያዙ ቅሬታዎችን አመራሩ ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ ተጠቁሟል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.