በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ምሽት 4 ሰዓት 30 ላይ ማንቼስተር ሲቲ ወደ ክራቨን ኮቴጅ አቅንቶ ከፉልሃም ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
በምሽቱ ጨዋታ ባለሜዳው ፉልሃም በሊጉ 3ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ሁሉንም አሸንፏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ቦርንማውዝ በሜዳው ቪታሊቲ ኤቨርተንን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱም ቡድኖች ካለፈው ሳምንት ሽንፈታቸው ለማገገም ጨዋታውን ለማሸነፍ የሚያደርጉት ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
በሌላ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ በሜዳው ሴንት ጀምስፓርክ ከቶተንሃም ሆትስፐር ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
በሊጉ ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ያደረገው ኒውካስል ዩናይትድ ተከታታይ 3ኛ ድሉን ለማሳከት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
ካለፉት አራት የሊጉ ጨዋታዎች ምንም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው ቶተንሃም ሆትስፐር በበኩሉ ወደ ድል ለመመለስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ኒውካስል ዩናይትድ ሦስቱን ሲያሸንፍ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ሊጉን አርሰናል በ30 ነጥብ ሲመራው ማንቼስተር ሲቲ በ25፣ ቼልሲ ደግሞ በ24 ነጥብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!