Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግናን ጉዞ ለመፋጠን በአሰሪዎች ተሳትፎና በሠራተኞች መብት መካከል ሚዛን መጠበቅ ወሳኝ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግናን ጉዞ ለመፋጠን የአሰሪዎችን ተሳትፎ በማሳደግና በሠራተኞች መብት አከባበር መካከል ሚዛን መጠበቅ ወሳኝ ነው አሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 37ኛው የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ የኢትዮጵያ መንግሥት ለዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት እንቅስቃሴና መርሆዎች በተለይም ሰላም፣ ክብር፣ ፍትህ፣ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎና ዓለም አቀፍ ህግጋትን በጥልቅ ያከብራል።
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ ውጤት እየተገኘበት የሚገኘው የሁሉም ዜጎች ጉልበትና አስተዋፅኦ በአንድነት በመተሳሰሩ ነው ብለዋል ።
በፌዴራልና በክልል መንግስታት በጋራ በተቋቋመው የሦስትዮሽ ምክር ቤት የአሰሪና የሰራተኛ ግንኙነትን ማሳደግ መቻሉንም ነው የገለጹት።
ሰራተኞች ተለዋጭ ኢኮኖሚና ሰላም የሰፈነበት ሀገር ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ አመልክተዋል፡፡
የዓለም አቀፍ የሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ሉክ ትሪያንግል በበኩላቸው፥ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች ብለዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሠራተኛ ማኅበራት መብቶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መሻሻል መኖሩን ጠቅሰው፥ ተቋማቸው የጋራ ግቦችን፣ ደህንነትን፣ ሰላምንና ማህበራዊ ፍትህን ለሁሉም ለማሳካት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል፡፡
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.