የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን (ቀይ ቀበሮዎቹ) ኬንያን በማሸነፍ ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ የደረጃ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኬንያን 3 ለ 0 አሸንፋለች፡፡
የቀይ ቀበሮዎቹን ግቦች ዳዊት ካሳው፣ ቢኒያም አብረሃ እና ብሩክ እይላቸው በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በዚህም መሰረት ውድድሩን በሦስተኛነት ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን፥ ከ22 ዓመታት በኋላ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ በፍጻሜው ታንዛኒያ ዩጋንዳ 9 ሰዓት ከ30 ይገናኛሉ፡፡