Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 ስድስተኛ ሳምንት ውድድር በመጪው ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተወዳዳሪዎች ጠንካራ ፉክክር ጋር የቀጠለው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 ስድስተኛ ሳምንት የድምጻውያን ውድድር በመጪው ቅዳሜም ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡

የበርካታ ባለተሰጥኦ ድምጻውያን መታያ የሆነው ፋና ላምሮት የምዕራፍ 21 ውድድር ለ13 ሳምንታት የሚካሄድ ሲሆን ÷ በየሳምንቱ ዳኞች በሙያቸው፣ ተመልካቾች ደግሞ ባልተገደበ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይዳኛሉ፡፡

የምድብ ሁለት ስድስት ተወዳዳሪዎች በቅዳሜው የስድስተኛ ሳምንት ውድድር ራሳቸው የመረጧቸውን ሁለት ሙዚቃዎች ከዛየን ባንድ ጋር ያቀርባሉ።

ዳኞች በእጣ የደረሷቸውን ሁለት ተወዳዳሪዎች አዘጋጅተው ለቅዳሜው ውድድር የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

የፋና ላምሮት ውድድር ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሳምንታት በራሳቸው፣ በዳኞች እና በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫዎች ነው የሚፈተኑት፡፡

በምዕራፉ ለፍጻሜ ለሚያልፉ 4 ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፥ ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ አራቱም የፍጻሜ ተፋላሚዎች ወደ 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

የፋና ላምሮት ውድድር ቅዳሜ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ በፋና በሁለቱም የቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ በፋና ዩትዩብ፣ ፌስቡክና የቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በ www.fanamc.com ለአድማጭ ተመልካቾች በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል፡፡

አድማጭ ተመልካቾች በውድድሩ እየተዝናኑ በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የዕለቱን የተወዳዳሪዎች መለያ ኮድ በመላክ ድምጽ መስጠት ይችላሉ፡፡

በለምለም ዮሐንስ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.