Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 26 ሺህ ቤቶችን ለማስገንባት ለሀገሪቱ የመጀመሪያ በሆነ የግንባታ ቴክኖሎጂ ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 26 ሺህ ቤቶችን ለማስገንባት ለሀገሪቱ የመጀመሪያ በሆነ የግንባታ ቴክኖሎጂ በዛሬው ዕለት ስራ አስጀምረዋል።

በዚህ ዓመት ከያዝናቸው ዋነኛ እቅዶች መካከል ቀዳሚው ለከተማችን ነዋሪዎች የቤት አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ነው ያሉት ከንቲባዋ÷ በዓመቱ ከ100 ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን በርካታ ተግባራትን እያከናወንን ብለዋል።

እቅዳችንን በጥራትና በፍጥነትን እውን ለማድረግ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን Cold-Formed Steel (CFS) የግንባታ ቴክኖሎጂን መጠቀም አንድ አማራጭ አድርገን ዛሬ ስራ አስጀምረናልም ነው ያሉት።

ቴክኖሎጂው በሌላው ዓለም የተለመደና ቤቶችንም ሆነ ህንፃዎችን በፋብሪካ ውስጥ የሚገጣጠሙ ብረቶችን በመጠቀም ወለልን፣ ግድግዳና ጣሪያን ጨምሮ ሁሉንም ክፍል በፍጥነትና በጥራት ማምረት የሚያስችል አሰራር መሆኑን አመላክተዋል።

የቴክኖሎጂው ፋብሪካ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መተከሉን ገልጸው÷ በፈጠራና ፍጥነት መርህ ግንባታን ከሳይት ወደ ፋብሪካ በመቀየር የግንባታ ፍጥነትን በማሳደግ፣ ወጪን በመቀነስና ጥራትን በማሻሻል አንጻር ተመራጭ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አስተዳደራችን እንደወትሮው የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ እና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በጠንካራ የፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ ዲስፕሊን እና በ24/7 የስራ መርሐ ግብር ፕሮጀክቱ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቆ ለታለመለት አላማ እንዲውል ያደርጋል ሲሉም ገልጸዋል።

ይህን ከከተማችን አልፎ ለሀገር ጠቃሚ የሆነ ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ይዘው የመጡትን የሌጋሲ ሆም ድርጅት ባለቤት ያሬድ አፈወርቅን (ኢ/ር) በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.