ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 37 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 37 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል አሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)።
የሚኒስቴሩ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ተጠሪ ተቋማቱ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ ባለፉት አራት ወራት በሁሉም ዘርፍ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።
የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ በተከናወነ ሥራ 1 ነጥብ 34 ሚሊየን በላይ የኦንላይን ምዝገባና ፈቃድ ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።
603 የንግድ ተቋማት ላይ የኢንስፔክሽን ሥራ መከናወኑን ጠቁመው፥ ከእነዚህ ውስጥም 59 የንግድ ድርጅቶች ላይ ርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
በሌላ በኩል ከመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 106 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን አመላክተዋል።
ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 84 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 3 ነጥብ 37 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ በተለይም ከእንስሳት ሃብት ተገቢውን ጥቅም እንድታገኝ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የገቢና ወጪ ምርት ጥራትን ለማረገጋጥ በተከናወነ ሥራ 1 ነጥብ 28 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የገቢ እና 134 ሺህ የወጪ ምርትና እቃዎች ላይ ቁጥጥር ተደርጓልም ነው ያሉት።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!