በጎንደር የሰላም ጥሪ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ከተማ እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጋራ ያዘጋጁት የሰላም ጥሪ የድጋፍ ሰልፍ በዛሬው እለት እየተካሄደ ነው።
በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው የሰላም ጥሪ ሰልፍ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በሰልፉ ላይ ሰላምን ለማጽናትና አብሮነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በዚህም የሀይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት ውይይት ግጭትን ለመፍታት ወሳኝ መሳሪያ ነው! ቤተእምነቶች ሰላም ማስፈን ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው! ሰላም፣ አንድነትና አብሮነት ከሐይማኖት ተቋም የተቀዱ ናቸው! የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።
በተጨማሪም ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአብሮነታችንና የጥንካሬዎቻችን መሰረቶች ናቸው! ሃይማኖት የሰላም መሰረት ነው! የሰላምና የመከባበር ባህልን ለማስቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ሚና የማይተካ ነው! በሚል መልዕክት በማስተላለፍ ህብረተሰቡ ለሰላምና አብሮነት ያለውን ፍላጎት አንጸባርቋል።
በምናለ አየነው