የቡና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር የገበያ አድማስን የማስፋት ጥረት …
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ኢትዮጵያ ቡና የማትልክባቸው ለነበሩ ሀገራት ቡና በመላክ የገበያ አድማሷን ማስፋት ችላለች አለ።
የባለሰልጣኑ ምክትል ዋና ዳሬክተር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ ሻፊ ኡመር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ የቡና ምርታማነትን በማሳደግ አረዓያነት ያለው ስራ እየተሰራ ይገኛል።
ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከ470 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጪ ገበያ በማቅረብ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውሰው፤ በ2018 በጀት ዓመት ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል።
በመሆኑም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት እመርታዊ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን በመጠቆም፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ 762 ሚሊየን ዶላር በማግኘት አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
ከምርምር ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ አዳዲስ የቡና ዝርያዎች ወደ ምርት እየገቡ እንደሆነ አንስተው፤ ዝርያዎቹ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን በመቋቋም ጥራት ያለው ከፍተኛ ምርት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታገጠም የማምረት ስራዎች እየተተገበሩ እንደሆነ እና ወደ መካናይዜሽን አመራረት እየተሸጋገርን እንገኛለን ነው ያሉት።
ከምርት ማሳደግ ጎን ለጎን የቡና ምርት መዳረሻ ገበያን ለማስፋት እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ነባር ገበያ ውስጥ ከመቆየት ባሻገር አዳዲስ ገበያዎች ውስጥ የመግባት ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ቡና የማትልክባቸው ለነበሩ ሀገራት ቡና በመላክ የገበያ አድማሷን ማስፋት ችላለች ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ ላይ ተፈላጊነቱ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ምርታማነትን በማሳደግ በዓለም ከፍተኛ የአረቢካ ቡና አቅራቢ ለመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቡና ጥራቱ ተጠብቆ እና በሕጋዊ ስርዓት ለውጪ ገበያ እንዲቀርብ እና የሀገር ኢኮኖሚን የሚደግፍ ሆኖ እንዲቀጥል ለማስቻል የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!