በፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ የሚታወቁ የአፍሪካ መሪዎች ልጆች በመዲናዋ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ የሚታወቁ የአፍሪካ መሪዎች ልጆች የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
ጎብኚዎቹ የአፍሪካ አንድነት እንዲኖር መሰረት ያስቀመጡ እና ለአፍሪካ አንድነት፣ ሰላም እና ልማት በፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ስራዎች የሚታወቁ ቀደምት መሪዎች ልጆች ናቸው።
በዚህ ጉብኝት የፓትሪስ ሉሙምባ ልጅ፣ የኔልሰን ማንዴላ የልጅ ልጅ፣ የኩዋሜ ኑኩሩማ ልጅ እና ሌሎችም የአፍሪካ ሕብረት መስራችና የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ጅማሮ ተሳታፊዎች ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በመዲናዋ በሚያደርጉት ጉብኝት የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ ብሔራዊ ቤተመንግስትን፣ የሳይንስ ሙዚየም እና የኮሪደር ልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ።
ጎብኚዎቹ ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መስፋፋት የነበራትን ሚና እና ያልተቋረጠ ተጋድሎ የሚያሳዩ ስራዎችን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተመልክተዋል።
ወላጆቻቸው ከቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎች ጋር የነበራቸውን ትብብር እና ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት የከፈለችውን ዋጋ በመመልከታቸው የተሰማቸውን ደስታም አጋርተዋል።
ጎብኚዎቹ በአርቲ አፍሪካ አዘጋጅነት ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት መርሐ ግብር ላይ መሳተፋቸው ይታወቃል።
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!