Fana: At a Speed of Life!

ለደቡብ ሀገራት ትብብር እና መጠናከር የቻይና ሚና

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና የደቡብ ሀገራት እድገትና ትብብር እንዲቀጥል የማደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ አለች፡፡

ሶስተኛው  የደቡብ ሀገራት ቲንክ ታንክ ትብብር ጉባኤ “ለአንድንት እና ጠንካራ ትብብር የደቡብ ሀገራት ሚና“ በሚል መሪ ቃል በቻይና ሻንጋይ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ቻይናን ጨምሮ ከ120 ሀገራት የተወጣጡ 350 ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ተመራማሪዎች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የአሰላሳይ ተቋማት ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የቻይናው ኮሙኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የሻንጋይ ማዘጋጃ ቤት ኮሚቴ ፀሀፊ ቼን ጂኒንግ በዚህ ወቅት÷ ከደቡብ ሀገራት ጋር ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ቻይና ከደቡብ ክፍለ ዓለም ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ታጠናክራለች ያሉት ቼን ጂኒንግ÷ ቻይና እና የደቡብ ሀገራት ለጋራ ራዕይ እና ስኬት በትብብር መስራታቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሃላፊ ሊዩ ሀይሲንግ በበኩላቸው÷ ቻይና ለታዳጊ የደቡብ ሀገራት ትብብር አንድነት እና ጥንካሬ መሪ እና አንቀሳቃሽ ሀይል ሆና መቆየቷን አንስተዋል፡፡

ሀገራቸው የደቡብ ለደቡብ ትብብር ኢኒሼቲቮች ተግባራዊነት እንደምትሰራ ገልጸው፤ የጋራ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ቻይና ከደቡብ ሀገራት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ ለመስራት ዝግጁ ናት ማለታቸውን ዥንዋ ዘግቧል።

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.