Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል – ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ስምምነቱ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል አሉ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ።

ትናንት በአማራ ክልል መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተፈረመውን የዘላቂ ሰላም ስምምነት አስመልክቶ ዋና ጸሐፊው እንዳሉት፤ ስምምነቱ ለክልሉ ሕዝብ ዘላቂ ሰላምንና እፎይታን የሚያመጣ ነው።

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ግጭቶች እንዲቆሙና ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ የተፈረመው ስምምነት ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባና እንዲሰራ ያደርጋል ብለዋል።

ስምምነቱ ችግሮችን በውይይት የመፍታትን ፋይዳ ያሳየ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተስተጓጉሎ የቆየው የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በመደበኛነት እንዲሳለጥ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።

ከሰላም የሚገኘው ትርፍ እልፍ ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፤ ለሁሉም ሰላምን ቀዳሚ ምርጫ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ስምምነቱ ዘላቂ ሰላም ለማጽናት መልካም ጅማሮ መሆኑን አንስተው፤ ሌሎች ቀሪ ኃይሎችም ይህንኑ ፈለግ በመከተል ምርጫቸው የሰላም መንገድና ሀሳብ ብቻ መሆን እንዳለበት ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከግጭት ይልቅ የውይይትና የሀሳብ ልዕልና ዘመን ተሻጋሪ ውጤት እንደሚያመጣ ጠቁመው፤ የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሰላም ስምምነቱ እንዲፈረም ላከናወኑት ተግባር አመስግነዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.