ለውጭ ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 46 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት 4 ወራት ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛንያ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 46 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል አለ።
የተቋሙ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም የጣቢያዎችን ኃይል የመሸከም አቅም ለማሳደግና የመቆጣጠሪያ ስዊቾችን በመቀየር ተጨማሪ ደንበኞችን እንዲያስተናግዱ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው÷ አዳዲስና ተጨማሪ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች የመቀየር ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
በተከናወኑት ስራዎች የአገልግሎት ጥራት በማሻሻልና ተደራሽነትን በማስፋት ተጠቃሚዎች ያለ ምንም ችግር አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
ተቋሙ የሚያመርተውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዋነኝነት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲሁም ከፍተኛ ኃይል ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች፣ ለኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር እና በማይኒንግ ዘርፍ ተሰማርተው ክፍያን በዶላር ለሚፈፅሙ አካላት እንደሚያቀርብ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ለውጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ፈላጊ ሀገራት የሚያቀርብ መሆኑንና በዋነኝነት ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛንያ መዳረሻዎች እንደሆኑ አመላክተዋል።
በዚህም በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 4 ወራት ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛንያ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 46 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸው÷ ይህም ከእቅዱ 25 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!