Fana: At a Speed of Life!

ሀዋሳ ከተማ እና መቻል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ እና መቻል 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኮሊንስ ኮፊ መቻልን መሪ ማድረግ የቻለ ሲሆን፥ የሀዋሳ ከተማን የአቻነት ግብ ጌታነህ ከበደ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሀድያ ሆሳዕና ከነገሌ አርሲ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ሲሆን፥ አርባ ምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና በዚሁ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ይጫወታሉ፡፡

ቀን 10 ሰዓት መቐለ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.