ኢትዮጵያውያን ከፋፋይ ትርክቶችን በመመከት ለዘላቂ ሰላምና ልማት ደጀን ሊሆኑ ይገባል – አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን ከፋፋይ ትርክቶችን በመመከት ለዘላቂ ሰላምና ልማት ደጀን ሊሆኑ ይገባል አሉ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)፡፡
በዱባይና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 20ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል፡፡
አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የለውጡ መንግስት ተግባራዊ ባደረገው እውነተኛ ፌዴራሊዝም ህዝብን ይበልጥ ማቀራረብ ተችሏል።
መንግስት ከ30 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ እየገነባቸው የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ተጨባጭ ስኬት የሚያሸጋግሩ ናቸው ብለዋል፡፡
እነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት እንደሚሳኩ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው መንግስት የጀመራቸው ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያሸጋግሩ በመሆናቸው በሙሉ አቅማቸው ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።