Fana: At a Speed of Life!

በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ለሚሳተፈው የልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ሽኝት ተደርጎለታል።

‎4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ከታህሳስ 1 እስከ 10/2018 ዓ.ም በአንጎላ ሉዋንዳ ይካሄዳል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በማሪዮት ሆቴል በተዘጋጀው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ስፖርተኞቹ በሚሳተፉበት የውድድር አይነት የኢትዮጵያን ስም እንደሚያስጠሩ ተናግረዋል፡፡

‎በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ ውድድር ላይ ከ70 በላይ አትሌቶች በሰባት የስፖርት አይነቶች ኢትዮጵያን ይወክላሉ።

‎በሙባረክ ፋንታው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.