Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን የ2018 የውድድር ዓመት የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ማስጀመሪያ እና የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት አከናውኗል፡፡

የ10ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው ውድድሩ ሚዛን አማን ከተማ ከፌደራል ማረሚያ በሚያደርጉት ጨዋታ ከመጪው ታህሳስ 18 ጀምሮ በተመረጡ ከተሞች የሚደረግ ሲሆን፥ የመጀመሪያው ዙር ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ይደረጋል።

ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ፣ ከምባታ ዱራሜ ከመቻል፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከኦሜድላ እና ባህር ዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ በመጀመሪያው ሳምንት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

መቐለ 70 እንደርታ የመጀመሪያው ሳምንት አራፊ ክለብ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በውድድር ዓመቱ መጨረሻ የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ ክለቦች በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ እንደሚደረግ በመድረኩ ላይ ተነስቷል።

ኢትዮጵያ በመጪው መጋቢት ወር የሚደረገውን የአፍሪካ የዞን አምስት የእጅ ኳስ ውድድርን እንድታዘጋጅ በአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ መመረጧ ይታወሳል።

በእንዳልካቸው ወዳጄ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.