Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ ከወልቭስ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ወልቭስን ይገጥማል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ሲሆን÷ በሦስቱ አቻ ተለያይቶ በአንዱ ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

ተጋጣሚው ወልቭስ በበኩሉ በዚህ የውድድር ዓመት አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም፡፡

ዩናይትድ በ22 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ወልቭስ በሁለት ነጥብ የሊጉ መጨረሻ ደረጃ 20ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሦስቱን ሲያሸንፍ ወልቭስ በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን 25 በማድረስ ከቼልሲ በግብ ክፍያ አንሶ 6ኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ መደረግ ይጀምራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.