Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል አሲዳማ አፈርን በማከም ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል አሲዳማ አፈርን በተለያዩ መንገዶች በማከም ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው አለ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ እንዳሉት ÷በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ለምነትን መጠበቅና መንከባከብ አስፈላጊ ነው።

የአፈር አሲዳማነት ምርታማነትን ከሚቀንሱ ተግዳሮቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቁመው÷አሲዳማ አፈርን በማከም ምርታማነትን ለማሳደግም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ መሰረትም በጥናትና ምርምር ለአሲዳማ የአፈር አይነቶች በሀገር ውሰጥ የሚዘጋጀውን ኦሲ-ማሳ የተሰኘ ማዳበሪያ በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ለአብነትም በክልሉ ሁላ ወረዳ ሉዳ ቀበሌ ኦሲ-ማሳ የተሰኘውን ማዳበሪያ የተጠቀሙ አርሶ አደሮች በአሲዳማ አፈር ላይ የዘሩት ስንዴ ውጤታማ እንደሆነ መጎብኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

መሰል የአፈር ማዳበሪያዎችን በስፋት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል ነው ያሉት፡፡

አሲዳማ አፈር ለኢትዮጵያ ግብርና መሻሻል ከፍተኛ ተግዳሮት ነው፤ ችግሩን ለመቅረፍም በጥናትና ምርምር በሀገር ውስጥ የተመረተው ኦሲ- ማሳ ማዳበሪያ ውጤታማ ነው ያለው ደግም ኦሲፒ ኢትዮጵያ ነው፡፡

ኦሲፒ ኢትዮጵያ ግብርናውን ለማዘመንና በእውቀት እንዲመራ ለማድረግ ላቦራቶሪ በማሟላት የአርሶ አደር ማሳ ድረስ እየወረደ ምርምር እያደረገ እንደሚገኝም ጠቅሷል፡፡

አርሶ አደሮች በበኩላቸው ለስንዴ ማሳ ኦሲ ማሳ የአፈር ማዳበሪያን በመጠቀም ምርታና ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.