Fana: At a Speed of Life!

ኢንተር ሚላን ከሊቨርፑል – የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ6ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ሊቨርፑል ወደ ጣሊያን አቅንቶ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ኢንተር ሚላንን የሚገጥም ሲሆን፥ ቼልሲ በተመሳሳይ ሰዓት ከሌላኛው የጣሊያን ክለብ አታላንታ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

የስድስት ጊዜ የመድረኩ ሻምፒዮን ሊቨርፑል ከኢንተር ሚላን ጋር ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች አራቱን በማሸነፍ የበላይነት ያለው ሲሆን፥ ኢንተር በ2ቱ ጨዋታዎች ድል ቀንቶታል፡፡

ባየርን ሙኒክ ከስፖርቲንግ ክለብ እንዲሁም ካይራት አልማቲ ከኦሎምፒያኮስ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ይገናኛሉ፡፡

ባርሴሎና ከኢንትራክት ፍራንክፈርት፣ ሞናኮ ከጋላታሳራይ፣ ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ኡኒየን ሴን ጂሎስ ከማርሴ፣ ቶተንሃም ሆስትፐርስ ከስላቪያ ፕራግ በተመሳሳይ 5 ሰዓት የሚደረጉ የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.