Fana: At a Speed of Life!

በየዓመቱ 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር ይከናወናል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዲጂታል ምህዳር በየዓመቱ 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር የዲጂታል የገንዘብ ዝውውር ይከናወናል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
2ኛው የኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፍረንስ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተገነባው የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረተ ልማት በቀጣይ ለሚሰራው የዘርፉ ሽግግር አጋዥ እና ተደማሪ አቅም ነው።
ከዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ መካከልም በፋይዳ መታወቂያ የተሰራው ስራ የተለያዩ ተቋማትን በማቀናጀት እየተገነባ ለሚገኘው ኢኮኖሚ ለዜጎች ተሳትፎ በር ሆኖ እያገለገ ይገኛል ብለዋል።
በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ አገልግሎት የዲጂታል ሽግግሩ ማሳያ መሆኑን ገልጸው፤ ለተቀላጠፈ እና ለዘመናዊ አገልግሎት አብነት መሆኑን አንስተዋል።
እስካሁን የተተገበሩትን መነሻ በማድረግ በቀጣይ ተጠቃሚነትን እና አካታችነትን በስፋት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
በመንግሥት የተጀመሩ የዲጂታል ሽግግር ስራዎችን ከግብ ለማድረስ ሁሉንም ባለድርሻዎች እና የማህበረሰብ ክፍሎችን በማካተት ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት።
የተጀመረውን የዲጂታል ሽግግር ከአቅርቦት ወደ ተጨበጠ ድርጊት፣ ለውጥ እና አጠቃላይ ሀገራዊ ብልጽግና ልናሸጋግረው ይገባል ሲሉ አመላክተዋል።
በኮንፍረንሱ ከፈረንጆች 2026 እስከ 2030 ለአምስት ዓመታት የሚተገበር የብሔራዊ ዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ይፋ ተደርጓል።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook WMCC
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.