የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ሊመራ የሚችል ስትራቴጂ ተቀርጾ እየተሰራ ነው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ሊመራ የሚችል ስትራቴጂ ተቀርጾ እየተሰራ ነው አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፡፡
2ኛው የብሔራዊ ዲጂታል ክፍያ ኮንፍረንስ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
በዚሁ ወቅት ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራ በኢትዮጵያ እንደሌሎች ታዳጊ ሀገራት ሰፊ ሥራ እየተሰራበት ነው።
የዲጂታል ፋይናንስ ምህዳር ሰፊ መሰረት እየያዘ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተመዘገበው ውጤት በቅንጅት በመሰራቱ የመጣ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በቀጣይም ጠንክረን በመስራት በጾታ፣ በገጠር እና በከተማ መካከል ያለውን የተጠቃሚነት ልዩነት ማሻሻል ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ አንደኛውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጠናቃ ሁለተኛውን መጀመሯን ገልጸው፤ የቀደሙ ልምዶች ቀጣዩን ምዕራፍ አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችላል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ከዚህ ዓመት ጀምሮ የሚተገበረው የአምስት ዓመት ስትራቴጂው ለኢኮኖሚ አፋጣኝ እና አካታች ጉልበት ይሆናል ነው ያሉት፡፡
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!