Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማቱ በከተማዋ ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን እየቀረፈ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን እየቀረፈ ነው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማዋ እየከተናወኑ የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገድና የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸውም ወቅት በከተማዋ በተለያዩ ወረዳዎች እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከዚህ ቀደም ሕዝቡ የሚያነሳቸውን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እየፈታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ማህበረሰቡም ለልማት ስራው ውጤታማነት እያደረገ የሚገኘው ቀና ትብብር ምቹ ሀኔታን የፈጠረ ነው ብለዋል።

በቀጣይ ከወረዳዎች በመቀናጀት ስራዎች በሚፈለገው የጥራት ደረጃና ፍጥነት ለማከናወን ርብርብ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችም በከተማው ከዚህ ቀደም ከእግረኛ መንገድ፣ ከፍሳሽ ማስወገጃና የመንገድ መብራቶች ችግሮችን እየቀረፈ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.