የግብፅ ሚዲያዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ዜጎችን ዋሽተዋል – ግብጻዊ አክቲቪስት
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብጽ ሚዲያዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሳሳች መረጃ በማቅረብ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር አሉ ግብጻዊው አክቲቪስት ሃምዲ ሱሌይማን፡፡
ከፋና አረብኛ ፖድካስት ጋር ቆይታ ያደረጉት ሃምዲ ሱሌይማን፥ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በግብፅ እና ሱዳን ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለው ተናግረዋል።
ግድቡ በዋነኛነት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨትና ኃይል ካመነጨ በኋላ ውሃው ተፈጥሯዊ ሂደቱን ጠብቆ ወደ ተፋሰስ ሀገራት የሚሄድ በመሆኑ ለግብጽም ሆነ ለሌሎች የተፋሰሱ ሀገራት ስጋት የለውም ነው ያሉት፡፡
ስለ ግድቡ መፍረስና ስለ ግብፅ የውሃ ደህንነት ስጋት የሚሰራጩ የስጋት መረጃዎች ትክክል እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለሰላም፣ ለትብብርና ከግብፅ ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመመስረት እውነተኛ ፍላጎት እንዳላት መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡
የግብጽ መንግሥት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሕዝቦችን የሚመለከትበት መንገድ ልክ እንዳልሆነም አስረድተዋል፡፡
ግብጻዊው አክቲቪስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ከኢትዮጵያ ይልቅ የአፍሪካ ፕሮጀክት አድርገው እንደሚመለከቱ አብራርተዋል፡፡
በዚህም የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ባላቸው የተፈጥሮ ሀብት ላይ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲሰጡ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
በግብፅ የአስዋን ግድብ የኑቢያ ነዋሪዎችን እንደሚያፈናቅልና ለበሽታ እንደሚያጋልጥ ገልጸው፥ ግድቡ የግብፅን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉን ጠቁመዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመላው አፍሪካ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ የባሕር በር በማግኘት የኢኮኖሚ ዕድገቷን ታጠናክራለች ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በግብርና እና በመሠረተ ልማት ዘርፍ ልማትን ለማፋጠን የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥረት መመልከታቸውንም ገልጸዋል።
በአህመድ አብዱልባር
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!