ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም በማካሄድ ለውጭ ባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ፈጥራለች – አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በማካሄድ ለውጭ ባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ፈጥራለች አሉ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)፡፡
አምባሳደር ጀማል (ዶ/ር) ከሀገሪቱ ኤስቢኬ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኩባንያ መስራችና ባለቤት ሼክ ሱልጣን ቢን ካሊፋ ቢን ዛይድ አልናህያን (ዶ/ር) ጋር በዱባይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ግዙፍ ኩባንያዎች መካከል የሚጠቀሰው SBK ቢዝነስ ግሩፕ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም ተገልጿል።
አምባሳደር ጀማል በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በማካሄድ ለውጭ ባለሃብቶች ምቹ እና ሳቢ የኢንቨስትመንት ከባቢ ፈጥራለች፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አማካኝነት የአፍሪካ የንግድ እና ሎጂስቲክስ ማዕከላዊ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗንም ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሃብቶች መንግሥት ያዘጋጃቸውን ዘርፈ ብዙ ማበረታቻ ፓኬጆች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ሼክ ሱልጣን ቢን ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ለማበረታታት የወሰደቻቸውን ርምጃዎች ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው ኩባንያው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኩባንያው ኢትዮጵያን እንደ ማዕከል በመጠቀም በቀጣናው ገበያ የራሱን ጉልህ ድርሻ ለመያዝ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለመለየት፣ ለማዋቀር እና ወደ መሬት መውረዱን ለመከታተል የሚረዳ የጋራ ቴክኒካል ቡድን ለማቋቋም ከመግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ መጠናቀቁን ኤምባሲው ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!