Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሟን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ደረጃ ጋር በማጣጣም ለመተግበር ቁርጠኛ ነች – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሟን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ደረጃ ጋር በማጣጣም ለመተግበር ቁርጠኛ ነች አሉ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኒውክሌር ኢነርጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ ሜካኤል ቹዳኮቭ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ የኒውክሌር ኢነርጂን የጋራ ትብብር በሚያጠናክሩ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኃይልና ቴክኖሎጂን ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪና ለምርምር ልህቀት ለመጠቀም ካላት ጽኑ አቋም በመነሳት እየሰራች ትገኛለች።

ለዚህም ሀገራዊ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራምን በቅርቡ መጀመሯን ገልጸው÷ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን በማቋቋም በይፋ ወደ ሥራ መግባቷን አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሟን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ደረጃና መመሪያዎች ጋር በማጣጣም ለመተግበርና በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኢትዮጵያ ከኒውክሌር ኃይል ስትራቴጂካዊ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ የጀመረችውን ጉዞ እውን ለማድረግ ሙያዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የተገለጸው፡፡

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.