ዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያቀደችውን ዓላማ እንድታሳካ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው – ራፋኤል ማርያኖ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያቀደችውን ዓላማ እንድታሳካ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው አሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማርያኖ ግሮሲ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም መጀመሯን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያ ኪሚሽኑን አቋቁማ ሥራ መጀመሯ ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን በመግለጽ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ራዕይና የአመራር ቁርጠኝነት ኢትዮጵያ ሰላማዊና ደኅንነቱ የተጠበቀ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም መጀመሯን አድንቀዋል፡፡
የኒውክሌር ኃይል የኢንዱስትሪ ዕድገትና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው÷ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ኤጀንሲው ኢትዮጵያ በዘርፉ ያቀደችውን ዓላማ እንድታሳካ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም ለአንድ ሀገር ዕድገት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው÷ ኢትዮጵያም የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን እየሰራች ያለው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም ላይ በትኩረት መሥራቷ ለወደፊት ዕድገቷ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበርክት ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም እንድትገነባ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!