Fana: At a Speed of Life!

“ጊፋታ” በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለኢትዮጵያ ጥልቅ ትርጉም አለው – ሰላማዊት ካሳ

አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወላይታ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል “ጊፋታ” በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለኢትዮጵያ ብሎም ለወላይታ ህዝብ ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ።
የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል “ጊፋታ” በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
ሚኒስትሯ በዓሉ በዩኔስኮ መመዝገቡን በማስመልከት በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ በበይነ መረብ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መንግስት የጊፋታን እሴቶች በትምህርትና በመገናኛ ብዙሃን በማስተዋወቅ ረገድ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን በመልዕክታቸው አንስተዋል፡፡
ለበዓሉ የተሰጠው እውቅና ለመላው ኢትዮጵያውያን ብሎም ለወላይታ ህዝብ ጥልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸው፥ ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርጋቸውን የጋራ ባህላዊ ብልጽግና ለማጠናከር ይረዳል ያሉት።
የጊፋታ በዓል ባህሉንና ስርዓቱን ጠብቆ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር መንግስት ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.