Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለጸረ ሙስና ትግል ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው – ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የጸረ ሙስና ኮንቬንሽን መሰረት ለጸረ ሙስና ትግል ልዩ ትኩረት ሰጥታ እሰራች ነው አሉ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)፡፡
ኮሚሽነሩ በ22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረሙስና ቀን አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ቀኑ የተቋማትን የጸረ ሙስና ትግል ለማሳደግ በልዩ ትኩረት መከበሩን ተናግረዋል።
በጸረ ሙስና ትግል ረገድ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ወጥነት ያለው ትግበራ፣ የአመለካከትና የተቋማት ጥንካሬ ጉድለት እንደሚስተዋል አንስተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ከለውጡ ወዲህ የጸረ ሙስና ትግልን ጉድለት በማረምና ሕጎችን በማሻሻል ሙስናን የመከላከል ሥራዎች መከናወናቸውን ነው ያብራሩት፡፡
በዚህም ተቋም እና ዘርፍ ተኮር ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው ÷ የፍትሕ እና የዳኝነት አካላትን አቅም የመገንባት ሥራን ለአብነት ጠቅሰዋል።
ከለውጡ ዓመታት በፊት በሥነ ምግባር ጉድለት አደጋ ተጋርጦባቸው የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን የመታደግ ሥራ ተከናውኗልም ነው ያሉት፡፡
በቀጣይ ለሕዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች፣ በመሬት አስተዳደር፣ በሰነዶች፣ በግዥዎች እና መሰል ዘርፎች ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።
ለውጤታማ ሀገራዊ የጸረ ሙስና ትግል የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግም ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.