ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሙስናን በመከላከል ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠው
አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሙስናን በመከላከል ረገድ ላበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠው።
22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ ምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል፡፡
በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን በመታገል ሒደት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ሰጥቷል።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንም በተለያዩ ዘገባዎች ሙስናን ለመታገል ባበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት እውቅና ተችሮታል።
በለይኩን አለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!