Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርስን ሥርቆትና ውድመት ለመከላከል…

አዲስ አበባ፣ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤሌክትሪክ ሃይል እና መሰረተ ልማት ላይ የሚደርስን ስርቆትና ውድመት ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር እንዳሉት ÷ በተለያዩ አካባቢዎች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርስ ሥርቆትና ውድመት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡

በተለይም የኃይል፣ የትራንስፎርመር ፣ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ ኬብል ስርቆት እንዲሁም በመኪና ግጭት የሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት በስፋት እንደሚስተዋል አስረድተዋል፡፡

ባለፉት 4 ወራት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ 107 ጉዳቶች መፈጸማቸውን ጠቁመው÷ ከእነዚህ ውስጥ 10 የወንጀል ክሶችን በመመስረት ጉዳዩ በፍርድ ሒደት ላይ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በምርመራ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈጸመ ስርቆት፣ ውድመትና የኃይል ስርቆት 143 ነጥብ 29 ሚሊየን በላይ ብር ጉዳት መድረሱን አቶ አንዋር ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

በመሰረተ ልማት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ከግለሰብና ከተቋም አልፎ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ የመሠረተ ልማት ጥበቃ ሥራን ለማጠናከር ከፍትሕ አካላትና ሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ነው የገለጹት፡፡

በኤሌክትሪክ ሃይል እና መሰረተ ልማት ላይ የሚደርስን ስርቆትና ውድመት ለመከላከልም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.