ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት አክትሟል አሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፡፡
የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ አብደላቲ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት ያወገዙት ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)÷ ግብጽ ሰላምና መረጋጋትን አደጋ ላይ ከሚጥሉ አፍራሽ ንግግሮችና ድርጊቶች መቆጠብ እንዳለባት አስገንዝበዋል።
ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታራምደው የቅኝ ግዛት ትርክት ማክተሙን ገልጸው÷ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ አቋም የተናጠል ርምጃ ነው ማለታቸው የዘመኑን እውነታ የማይመጥን የቅኝ ግዛት እሳቤ ነው ብለዋል።
በናይል ወንዝ እኔ ብቻ የበላይነቱን ልውሰድ የሚል ጊዜ የግብጽ ያለፈበት ትርክት ተቀባይነት እንደሌለው አንስተው÷ መሰል እሳቤዎች ከሀገር ባለፈ ቀጣናዊ መረጋጋትን ስጋት ውስጥ የሚከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አስተያየቱ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚቃረን ተቀባይነት የሌለው ሐሳብ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የናይል ወንዝ አብዛኛውን ድርሻ የምትወስደው ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ህጋዊ መብት እንዳላት ጠቁመው÷ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሕጋዊና በመርህ ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን የኢትዮጵያ መብት እውቅና እየሰጠው ይገኛልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!