Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ይሰራል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

‎አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሶስት ዘመናዊ ባለ 10 ወለል ስማርት የወረዳ የአስተዳደር ሕንጻዎችን በዛሬው ዕለት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማሻሻል በከተማዋ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡

ለአብነትም የወረዳ አገልግሎት መስጫዎችን ማዘመን፣ በበቂ የሰው ኃይል ማደራጀት፣ በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ እንዲሁም ለአገልግሎት ሰጪውና ለተገልጋዩ ማሕበረሰብ ምቹ የሥራ ቦታን መፍጠርን አንስተዋል፡፡

በዚህም በልደታና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተሞች በሶስት ወረዳዎች የወረዳ አስተዳደር አገልግሎትን ማዘመን የሚያስችሉ ስማርት ሕንጻዎች ግንባታ ተጠናቅቆ ሥራ መጀመሩን ገልጸዋል።

ሕንጻዎቹ አገልግሎትን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት የተገልጋዩ ጊዜና ሃብት ሳይባክን እንግልትን በመቀነስ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስችላሉ ነው ያሉት፡፡

ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ፣ የልጆች ማቆያና መጫወቻ ስፍራ፣ ውብ፣ ጽዱና አረንጓዴ ቅጥር ጊቢ በውስጣቸው እንደያዙ አመልክተዋል።

በተጨማሪም አካል ጉዳተኞችንና አቅመ ደካሞችን ታሳቢ ያደረጉ ሊፍቶች የተገጠሙላቸው መሆናቸውን ከንቲባዋ ጠቁመዋል።

ስማርት ሕንጻዎቹ አዲስ አበባን ስማርት ለማድረግ የተጀመረው ሥራ አካል መሆናቸው አንስተው ÷ በቀሪዎቹ ወረዳዎች ላይ የማስፋትና የማብዛት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.